am_2ch_text_ulb/25/09.txt

1 line
619 B
Plaintext

\v 9 አሜስያስም ለእግዚአብሔር ሰው፦" ለእስራኤል ሠራዊት ስለሰጠሁት መቶ መክሊትስ ምን እናደርጋለን?" አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሰውም፦ "እግዚአብሔር ከዚያ እጅግ የበለጠ ሊሰጥህ ይችላል" ብሎ መለሰለት፡፡ \v 10 በመሆኑም አሜስያስ ከኤፍሬም ወደርሱ የመጡትን ሠራዊት ለይቶአቸው እንደገና ወደ ቤት ላካቸው፡፡ ስለዚህም በይሁዳ ላይ ቁጣቸው እጅግ ነደደ፤ ወደ ቤትም በጋለ ቁጣ ተመለሱ፡፡