am_2ch_text_ulb/21/08.txt

1 line
704 B
Plaintext

\v 8 በኢዮራም ዘመን ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ ዐመፀ፤ በራሳቸውም ላይ ንጉሥ ሾሙ፡፡ \v 9 በዚያን ጊዜ ኢዮራም ከአዛዦቹና ከሠረገላዎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እርሱንና የሠረገላዎቹን አዛዦች ከብበው የነበሩትን ኤዶማውያንን መታ፡፡ \v 10 በመሆኑም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ እንዳመፀ ነው፡፡ ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለተወ የልብና ከተማ ጭምር በዚያው ጊዜ በኃይሉ ላይ ዐመጸ፡፡