am_2ch_text_ulb/09/22.txt

1 line
560 B
Plaintext

\v 22 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን ከዓለም ነገሥታት ሁሉ በባለጠግነትና በጥበብ በለጠ፡፡ \v 23 ምድር ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰለሞንን መገኘት ይፈልጉ ነበር፡፡ \v 24 ከዓመት ዓመት የሚጎበኙትም ግብር፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች፥ አልባሳት፥ የጦር መሣሪያዎች እና ቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ፈረሶችና በቅሎዎችን ያመጡ ነበር፡፡