am_2ch_text_ulb/09/07.txt

1 line
614 B
Plaintext

\v 7 "ጥበብህን ስለሚሰሙ ህዝብህ ምንኛ የተባረኩ፥ ዘወትር በፊትህ የሚቆሙ አገልጋዮችህም ምንኛ የተባረኩ ናቸው፡፡ \v 8 ለአምላክህ እግዚአብሔር ንጉሥ ትሆን ዘንድ ባንተ ደስ የተሰኘ እና በዙፋን ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ብሩክ ይሁን፡፡ አምላክህ እስራኤልን ለዘላለም ያፀናቸው ዘንድ ስለወደደ ፍትህንና ጽድቅን እንድታደርግላቸው በላያቸው ላይ አነገሠህ " አለችው፡፡