am_2ch_text_ulb/03/01.txt

1 line
700 B
Plaintext

\c 3 \v 1 ከዚህ በኋላ ሰለሞን እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠለት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመረ፡፡ ዳዊት እንዳቀደለት በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ሥፍራውን አዘጋጀ፡፡ \v 2 በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር በሁለተኛው ቀን መሥራት ጀመረ፡፡ \v 3 ሰለሞንም ለእግዚአብሔር ቤት የጣለው መሠረት ስፍሮች እነዚህ ናቸው፡፡ ርዝመቱ በድሮው መለኪያ ስልሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡