am_2ch_text_ulb/13/19.txt

1 line
808 B
Plaintext

\v 19 አብያ ኢዮርብዓምን አሳደደ፤ ከእርሱም ከተሞችን ወሰደ፤ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ፤ \v 20 ኢዮርብዓምም በአብያ ዘመን እንደገና ኃይሉ ከቶም አላገገመም፡፡ እግዚአብሔርም ቀሰፈው፤ እርሱም ሞተ፡፡ \v 21 አብያ ግን በረታ፤ ለራሱ አስራ አራት ሚስቶችን ወሰደ፤ ሃያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና አስራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ \v 22 የተቀሩት የአቢያ ድርጊቶችና ባሕርዩ የተናገራቸው ነገሮችም በነቢዩ አዶ ትርጓሜ/አንድምታ ተጽፈዋል፡፡