am_2ch_text_ulb/02/01.txt

1 line
686 B
Plaintext

\c 2 \v 1 በዚህ ጊዜ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤት እንዲገነባ እና ለመንግሥቱ ቤተ መንግሥት እንዲገነባ አዘዘ፡፡ \v 2 ጭነት የሚሸከሙ ሰባ ሺህ ሰዎች እና ከተራሮች እንጨት የሚቆርጡትን ሰማንያ ሺህ ሰዎች እነርሱንም የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች መደበ፡፡ \v 3 ሰለሞንም ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ፦የሚኖርበትን ቤት እንዲሠራ የዝግባ እንጨት በመላክ ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ ለእኔም እንደዚሁ አድርግልኝ፡፡