am_2ch_text_ulb/01/02.txt

1 line
985 B
Plaintext

\v 2 ሰለሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለዳኞችም፥ በመላው እስራኤልም ሁሉ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ፤ \v 3 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በገባኦን ስለነበር ሰለሞንና ጉባኤው ሁሉ እዚያ ወደነበረው የአምልኮ ሥፍራ ሄዱ። \v 4 ዳዊት ግን ለእግዚአብሔር ታቦት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ስለነበር ከቂርያት ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ሥፍራ አምጥቶት ነበር። \v 5 በተጨማሪም በሆር ልጅ በኡሪ ልጅ በባስልኤል የተሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ነበረ፤ ሰለሞንና ጉባኤውም ወደ እርሱ ሄዱ።