am_2ch_text_ulb/05/13.txt

1 line
815 B
Plaintext

\v 13 መለከቱን የሚነፉትና መዘምራኑም ከመቅደሱ ሲወጡ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያወደሱ በአንድ ቃል ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ ከመለከቶቹና ከጸናጽሎቹ ከሌሎቹም መሳሪያዎች ጋር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡" ቸር ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚጸና ነውና" ብለው ዘመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቤቱ የእግዚአብሔር ቤት በደመና ተሞላ፡፡ \v 14 የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ከደመናው የተነሳ ካህናቱ ለማገልገል መቆም አልቻሉም ነበር፡፡