am_2ch_text_ulb/06/14.txt

1 line
548 B
Plaintext

\v 14 እንዲህም አለ፦ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ በፍጹም ልባቸው በፊትህ ከሚሄዱ ባሪያዎችህ ጋር ኪዳንንና የቃል ኪዳን ታማኝነትን የምትጠብቅ በሰማይም ሆነ በምድር እንዳንተ ያለ አምላክ የለም፤ ለባሪያህ \v 15 ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ አንተ፥ አዎ በአፍህ የተናገርኸውን ዛሬም እንደሆነው በእጅህ ፈጽመኸዋል፡፡