\v 10 ከሮብዓም ጋር ያደጉት ወጣቶች ተናገሩት፦ "'አባትህ ሰለሞን ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን ልታቀልልን ይገባል' ብለው ለነገሩህ ሰዎች፦ 'ትንሿ ጣቴ ክአባቴ ወገብ ትወፍራለች' ልትላቸው ይገባል፡፡ \v 11 "በመሆኑም አሁን ምንም እንኳን አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ የነበረ ቢሆንም እኔ ቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡