\v 15 ንጉሡም ሰለሞን በጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትልልቅ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ገብቶባቸው ነበር፡፡ \v 16 ከጥፍጥፍ ወርቅም ሦስት መቶ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዱም ጋሻ ውስጥ ሦስት ምናን ወርቅ ገብቶበት ነበር፡፡ ንጉሡም በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡