\v 20 ሕዝቅያስም ይህንን በይሁዳ ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት መልካም፥ ትክክለኛና ታማኝ ነገርን አከናወነ። \v 21 በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በጀመረው በየትኛውም ሥራ በሕጉና በትዕዛዛቱ አምላኩን ለመፈለግ በሙሉ ልቡ አከናወነው፤ እርሱም ተሳካለት።