\v 24 ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ሲነሱ ወደ አንተ ቢመለሱ፥ በዚህም ቤተ መቅደስ ውስጥ በፊትህ ስምህን ቢጠሩ፥ ቢጸልዩና ምህረትን ቢለምኑ \v 25 እባክህን ከሰማያት ስማና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሳቸው፡፡