\v 7 አሁንም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት መስራት በአባቴ በዳዊት ልብ ነበር፡፡ \v 8 ነገር ግን እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ "ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በልብህ ነበረ፤ ያ በልብህ የነበረ መሆኑ መልካም አደረግህ፡፡ \v 9 ነገር ግን ቤቱን አንተ ልትገነባው አይገባም፤ ይልቁንም ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራልኛል" አለው፡፡