am_2ch_text_ulb/07/04.txt

1 line
845 B
Plaintext
Raw Normal View History

\v 4 ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡ \v 5 ንጉሥ ሰለሞንም ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች በጎችና ፍየሎች ሰዋ፡፡ እንደዚህ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ፡፡ \v 6 ካህናቱም እያንዳንዳቸው በሚያገለግሉበት ቦታ ቆመው ሌዋውያኑም "የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" በሚለው መዝሙር እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ንጉሥ ዳዊት ያዘጋጀውን የእግዚአብሔር የዜማ መሳሪያዎች ይዘው ቆመው ነበር፡፡ ካህናቱ ሁሉ በፊታቸው መለከቶቻቸውን ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆሙ፡፡