am_2ch_text_ulb/04/11.txt

1 line
823 B
Plaintext
Raw Normal View History

\v 11 ኪራምም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹንና መሠዊያውን መርጪያ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡ ኪራምም እንደዚህ ለንጉሥ ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ - \v 12 ሁለቱን አዕማድ፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ጨረሰ፡፡ \v 13 በአዕማዱ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ለሚሸፍኑት ሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ተርታ ሮማኖች አድርጎ ለሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች አራት መቶ ሮማኖች ሠራ፡፡