# ተራሮች ከፍ ይላሉ፣ ሸለቆችም ይስፋፋሉ እዚህ ስፍራ ዘማሪው የሚናገረው፤ ተራሮች እና ሸለቆዎች ራሳቸውን ለማንቀሳቀስ የፈቀዱ ይመስል እግዚአብሔር እንዲንቀሳቀሱ እና እንዲለወጡ ማድረጉን ነው፡፡ እነርሱ በዚህ መንገድ የተገለጹት በእግዚአብሔር ሀይል ላይ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # እንዳያልፉ ድንበር አበጀላቸው እዚህ ስፍራ ዘማሪው እግዚአብሔር ውሆች እርሱ የፈጠረላቸውን ድንበራቸውን እንዳያልፉ ማድረጉን የገለጸው ውሆች ራሳቸው ድንበራቸውን ላለማለፍ እንደመረጡ አድርጎ ነው፡፡ እነርሱ በዚህ መንገድ የተገለጹት እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ያለውን ስልጣን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ሊያልፉት/ሊያቋርጡት የማይችሉት ድንበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ድንበር ዳርቻ # ለእነርሱ "እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ውሆችን ነው፡፡