# መንበርከክ ብዙውን ጊዜ መሸነፍን ለማሳየት ሁለቱንም ጉልበቶች በመሬት ላይ ማድረግ፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ) # የእርሱ የመሰማሪያው ህዝብ "መሰማሪያ" የሚለው ቃል እንስሳት በሚሰማሩበት ስፍራ ስለሚያገኙት ምግብ ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን ይህም ደግሞ በተራው ያህዌ ለህዝቡ ለሚያደርገው አቅርቦት ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "እኛ የሚያስፈልገንን የሚያሟላን ህዝቡ ነን" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ) # መሰማሪያ እንስሳት ለመጋጥ ሳር የሚያገኙበት አካባቢ # የእጁ በጎች እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እረኛ በጎችን እንደሚጠብቅበት መንገድ ያህዌ እንዴት ህዝቡን እንደሚጠብቅ ነው፡፡ "እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ እርሱ የሚጠብቃቸው ህዝቦች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # ዛሬ እነሆ፣ የእርሱን ድምጽ ትሰማላችሁ! "እነሆ፣ ዛሬ ድምጹን ትሰማላችሁ!" ዘማሪው ይሁነኝ ብሎ የሚናገረውን ይተረጉመዋል፡፡ # የእርሱን ድምጽ ስሙ እዚህ ስፍራ "የእርሱ ድምጽ" የሚለው የሚወክለው የእግዚአብሔርን ንግግር ወይም እርሱ የተናገረውን ነው፡፡ "እግዚአብሔር ሲናገር አድምጡ" ወይም "እግዚአብሔር የሚናገረውን ስሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)