# የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? ሙሴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው የእሥራኤልን ሕዝብ ለመገሰፅ ነው፡፡ይሄ አሕፅሮተ ሥም በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንደገና መተላለፍ የለባችሁም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ) # እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለም እነርሱን ማገዝ ከእነርሱ ጋር እንደመኖር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔር አይረዳችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # በጠላቶቸችሁ ፊት እንዳትወድቁ ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ጠላቶቻችሁ ድል እንዳይነሷችሁ ለመከላከል” ወይም “በጠላቶቻችሁ ላይ ድልን እንድታገኙ ለማድረግ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ) # በሰይፍ ትወድቃላችሁ እዚሀ ላይ “ሠይፍ”የሚያመለክተው ጦርነትን ነው፡፡“በጦርነት ውስጥ ትሞታላችሁ”ወይም “ከእነርሱ ጋራ ስትዋጉ ይገድሏችኋል” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ) # እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔርን መታዘዝ እርሱን እንደ መከተል ተደርጎ የተገለፀ ሲሆን የሚናገረውን ቃል አለመፈፀም ደግሞ ከእርሱ እንደመመለስ ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔርን መታዘዝ አቁማችኋል”ወይም “እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ ወስናችኋል” “(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)” # ከእናንተ ጋር አይሆንም እነርሱን ማገዝ ከእነርሱ ጋር እንደመኖር ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“አይረዳችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)