# የናቀው የእኔን መሐላ፣ ያፈረሰውም የእኔን ቃል ኪዳን አይደለም? አዎንታዊው ምላሽ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ዋነኛ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የኢየሩሳሌም ንግሥ የናቀው የእኔን መሐላ፣ ያፈረሰውም የእኔን ቃል ኪዳን ነበር”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት) # ቅጣቱን በራሱ ላይ አመጣለሁ “በራሱ ላይ አመጣለሁ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም ይህንን ቅጣት ይቀበላል ማለት ነው። ይህንን የአነጋገር ዘይቤ በሕዝቅኤል 11፡21 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የቅጣቱን መከራ እንዲቀበል አደርገዋለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት) # በእርሱ ላይ መረቤን እዘረጋለሁ፣ በማጥመጃ መረቤም ይያዛል እግዚአብሔር ንጉሡን በመረብ የሚያጠምደው በሚመስልበት ሁኔታ የጠላት ሰራዊት ንጉሡን እንዲይዙት እንደሚያስችላቸው ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # በማጥመጃ መረቤ ይያዛል ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በማጥመጃ መረቤ እይዘዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት) # ጥገኞቹ ሁሉ . . . ሰራዊት በሰይፍ ይወድቃል “መውደቅ” የሚለው ቃል “መሞት” ለሚለው የለዘበ ቃል ነው። እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚለው ቃል በሰይፎቻቸው ሰዎችን የሚገድሉ ወታደሮችን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ወታደሮች ጠገኞቹን ሁሉ . . . ሰራዊቱን ይገድሏቸዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # የተረፉትም በየአቅጣጫው ይበተናሉ ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሕይወት የተረፉት በየአቅጣጫው ይሸሻሉ” ወይም “በሕይወት የሚተርፉትን የጠላት ወታደሮች በየአቅጣጫው ይበትኗቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት) # እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ እግዚአብሔር ሰዎች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ ብሎ በሚናገርበት ጊዜ እርሱ ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለው ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ሰዎች ያውቃሉ ማለቱ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እውነተኛው አምላክ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ትረዳላችሁ” ወይም “ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለኝ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ትገነዘባላችሁ”