# አጠቃላይ መረጃ ያህዌ ለሕዝቡ መናገር ቀጥሏል፡፡ # ለሰሜን… በል፤ ለደቡብ… በል በእነዚህ ቦታዎች ያሉትን ሕዝቦች እያዘዘ ያለ ይመስል ያህዌ ለ‹‹ሰሜን›› እና፣ ለ‹‹ደቡብ›› ይናገራል፡፡ # ወንዶች ልጆቼ… ሴቶች ልጆቼ የእርሱ የሆኑት የእርሱ ልጆች እንደሆኑ ያህዌ ይናገራል፡፡ # በስሜ የተጠራው ሁሉ በአንድ ሰው ስም መጠራት የዚያ ሰው መሆንን ያመለክታል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በስሜ የተጠራ ማንኛውም ሰው›› ወይም፣ ‹‹የእኔ የሆነ ሁሉ›› # የሠራሁት፣ አዎን ያበጀሁት ሁለቱም ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፤ የእስራኤልን ሕዝብ የሠራ እግዚአብሔር መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡