# አጠቃላይ መረጃ እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል፡፡ # እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፣ እናንተም በቅርብ ያላችሁ የእኔን ኃይል እወቁ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ለማለት በሩቅ እና በቅርብ የሚሉትን ቃላት ይጠቀማል፡፡ ኃይል የሚለው ቃል ኃያል በሚል ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቦች ሁሉ በሁሉ ስፍራ ያደረግሁትን ስሙ ኃያል መሆኔንም እውቁ' (ስዕላዊ ንግግርና የነገር ስም ተመልከት) # አምላክ የለሾቹን መንቀጥቀጥ ያዛቸው ይህ የአምላክ የለሾቹ መንቀጥቀጥን በሚመለከት መንቀጥቀጣቸው የያዛቸው ጠላት እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አት፡- "አምላክ የለሾቹ በመንቀጥቀጥ ተዋጡ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት) # ከእኛ መካከል … ከምትነድድ? በጽዮን የሚገኙ ኃጢአተኞች እነዚህን ጥያቄዎች እንደጠየቁ ተመላክቷል፡፡ አት "እንዲህ አሉ፣ ‘ከእኛ መካከል … ከምትነድድ?’ ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት) # ከምትባላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? እነዚህ አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች በመሠረቱ አንድ ትገሩም ያላቸው ሲሆን ማንም ከእሳት ጋር መኖር እንደማይችል አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አት፡- "ማንማ ከሚበላ እሳት ጋር መኖር አይችልም! ለዘላለም ከምትነድድ ጋር ማንም መኖር አይችልም!' ወይም "ማንም የእግዚአብሔርን ፍርድ ታግሦ መኖር አይችልም፣ እንደ ዘላለማዊ እሳት ነውና' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት) # በጊዜያዊነት መቀመጥ ቤቱ ባልሆነ አንድ ቦታ መኖር