am_tn/psa/069/018.md

16 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ታደገኝ
ጸሐፊው እግዚአብሔር ሊታደገውና ነፃነቱን ሊመልስለት እንደሚችል ባሪያ እንደሆነ ራሱን በማሰብ እግዚአብሔርን እንዲታደገው ይጠይቀዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነፃ አውጣኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
# ተቤዠኝ
ጸሐፊው ነፃ ለመውጣት እዳው ሊከፈልለት የሚቻል እስረኛ እንደሆነ ራሱን በማሰብ እግዚአብሔርን እንዲቤዠው ይጠይቀዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አድነኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
# ስድቤን፣ እፍረቴን እና ውርደቴን
እነዚህ ረቂቅ ስሞች እንደ ድርጊት ሊብራሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች እንዴት እንደሰደቡኝ፣ እንዳሳፈሩኝ እና እንዳዋረዱኝ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
# ጠላቶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸው
እዚህ ላይ “በፊትህ” የሚለው እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ሁሉን ያያል ደግሞም ያውቃል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቼ ሁሉ እነማን እንደሆኑ አንተ ታውቃቸዋለህ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)