am_tn/isa/53/12.md

20 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አጠቃላይ መረጃ
ያህዌ ስለ ባርያው መናገር ቀጥሏል፡፡
# ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋር እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውንም ከብዙዎች ጋር ይከፋፈላል
ሁለቱም ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ‹‹ድርሻ›› እና ‹‹ምርኮ›› ጦርነት በድል ከተጠናቀቀ በኃላ አንድ ንጉሥ የተዘረፈውን መካፈል ወይም ለወታደሮች መሸለምን ያመለክታሉ፡፡ ይህም ማለት ከመሥዋዕቱ የተነሣ ያህዌ ባርያውን እጅግ ያከብረዋል ማለት ነው፡፡
# ብዙዎች
ብዙ ቅጂዎች ይህን፣ ‹‹አያሌ›› ወይም፣ ‹‹ብርቱዎች›› በማለት ተርጉመዋል፡፡
# ራሱን ለሞት ስላጋለጠ
‹‹መጋለጥ›› ምቹ መሆን ወይም ያለ ምንም ከለላ ማለት ነው፡፡ የያህዌ ባርያ ራሱን የሚሞትበት ሁኔታ ውስጥ አኖረ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፈቃደኝነት ለሞት መጋለጥን ተቀበለ››
# ከሕግ ተላላፊዎች ጋር ተቆጠረ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች እንደ ወንጀለኛ እንዲቆጥሩት ፈቀደ››