16 lines
1.2 KiB
Markdown
16 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# አጠቃላይ መረጃ
|
||
|
|
||
|
ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡
|
||
|
|
||
|
# በዐይኔ ፊት ብርቅና ክቡር ስለሆንህ
|
||
|
|
||
|
‹‹ብርቅ›› እና፣ ‹‹ክቡር›› የተሰኙት ቃሎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ያህዌ ሕዝቡን ምን ያህል እንደሚወድ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእኔ ዘንድ በጣም የተወደድህ ስለሆነ››
|
||
|
|
||
|
# ስለዚህ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ
|
||
|
|
||
|
ሁለቱም ሐረጐች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ በአንተ ፈንታ ጠላት ሌሎች መንግሥታትን ድል እንዲያደርግ አደርጋለሁ››
|
||
|
|
||
|
# ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ አንተንም ከምዕራብ እሰበስባለሁ
|
||
|
|
||
|
‹‹ምሥራቅ›› እና ‹‹ምዕራብ›› የተሰኙት አቅጣጫዎች ከሁሉም ቦታ ማለት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተንና ልጆችህን ከሁሉም ቦታ አመጣለሁ››
|